top of page
IMG-3218.jpg
የማህበሩ አስተዋጽዎች
  1. ማኅበራችን በኢትዮጵያ የሚገኘውን የአርብዓ ሐራ ገዳም ሕንፃውን ለማሠራት ከወሰደው ሠላሳ ሦስት ሚሊዮን ውስጥ በአማካይ ከ25% በላይ ለግሷል። 

  2. በተመሳሳይ መልኩ ድንቅ የተባሉት የቤተመቅደሱ ስዕሎች (በሙሉ ማለት ይቻላል) ወጪአቸውን የሸፈንነው ይሄው  ማኅበር ነው።

  3. አሁን በጅምር ላይ ያለው የጸበልተኞች ማረፊያ (ምድርና ፎቅ) የሚሠራው በእኛው አበረታችነት ነው። ከገዳሙ ራቅ ብለው ምንም አቅም ወይም ገቢ የሌላቸው ዘጠኝ አድባራት ይገኛሉ በዚህም ከገዳሙ ጋር ባደረግነው ምክክር መጠነኛ ድጎማ እንዲደረግላቸው ተደርጓል።

  4. በየወሩ የመድኃኔዓለም ዕለት በመላው አሜሪካ የሚገኙት ማኅበርተኞች የሚሳተፉበት የጸሎት መርሓ ግብር       በቴሌኮንፍረንስ ያካሄዳል።

  5. በአካል መገኘት ለሚችሉ ማኅበርተኞች ወርሃዊ የጸሎትና የዝክር መርሐግብር በመካነ ሰላም ቅዱስ ሚካኤል         ወቅድስት ኪዳነ ምሕረት ቤተክርስቲያን ያደርሳል።

bottom of page