top of page
7.png
IMG-3218.jpg

የምስካበ ቅዱሳን አርብዓ ሐራ መድኃኔዓለም የአጭር ገዜ እቅድ።

1.  እንደ ኢትዮጵያ አቆጣጠር 2016 ዓ.ም
2. የማኅበርተኞችን ቁጥር 400 ለማድረስ ጥረት ማድረግ።

3. የአባላቱን እርስበርስ ቤተሰባዊ አንድነትን ማጠናክር።

3. ለማኅበርተኞች ልዩ ልዩ መንፈሳዊ አገልግሎት መስጠት።

4. ማኅበሩን ይበልጥ ለማስተዋወቅ እንዲረዳ የሕዝብ ግንኙነትና የሚዲያ ንዑስ  ኮሚቴ ማዋቀር ሲሆን ለዚህም እንቅስቃሴ እየተደረግ ነው። 

Marble Surface

የማኅበራችን የረጅም ጊዜ ዕቅድ

 

ከዳላስ ከተማ ወጣ ብሎ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስትያንን ትውፊትና ሥርዓትን የጠበቀና በዚህም ምዕመናን፤

1. በጾም፣ በጸሎትና በአርምሞ ከፈጣሪያቸው ጋር የሚገናኙበት፤

2. መንፈሳዊ ህይወታቸውን የሚያድሱበት፤

3. ሕመምተኞች የሚፈወሱበትና የተጨነቁ የሚጽናኑበትና ፣እንዲሁም

4. የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያንን ገዳማዊ ሥርዓት ለምንኖርበት ሀገር ለማስተዋወቅ በሚያስችል መልኩ ከዳላስ ከተማ ወጣ ብሎ ለአንድ ሰዓት ያህል የሚያስነዳ ቦታ ላይ ከዚህ በታች የተጠቀሱትን አገልግሎቶች የሚያካትት ገዳም እንደ ልዑል እግዚአብሔር ፈቃድ ለማቋቋም ታስቧል።      


❖ የፀበል ቤቶች (ለወንዶችና ለሴቶች የተለያዩ)
❖ የገዳሙ ቋሚ አገልጋዮች ካሕናት መኖሪያና የእንግዶች ካሕናት ማረፊያ ቤቶች
❖ የፀበልተኞች ማረፊያ ክፍሎች
❖ ተግባር ቤት (ማዕድ ቤት) ከነ አዳራሹ
❖ ቤተመቅደስ ከነቤተልሔሙ
❖ የከብትና የንብ ዕርባታ ቦታ
❖ የአትክልትና የፍራፍሬ ልማት ቦታ
❖ በዕቅድ የሚተከሉ ለማኅበርተኞች መታሰቢያነት የሚያገለግሉ ዛፎች
❖ የመቃብር ሥፍራ
❖ ቤተመዘክር (ሃይማኖታችንን በደማቸው ያለመለሟት የሚታሰቡበት)
❖ ለልጆች አዳሪ ት/ቤት (በበጋ ወቅት ልጆች በገዳሙ ቆይታ አድርገው ሃይማኖታቸውን፣ ባሕላችውንና ታሪካቸውን የሚማሩብት)
❖ የአዛውንት መጦሪያ ክፍሎች ናቸው።

​     የገዳሙን ንድፈ ሐሳብ ለማየት እዚህ ይጫኑ

bottom of page