top of page
9999-1.png
ትምህርተ ሀይማኖት
ሚስጥረ ሥላሴ

የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ዓለም ከመፈጠሩ በፊት የነበረ፤ ያለና የሚኖር አንድ አምላክ መኖሩን ታምናለች፡፡ ይኸውም አንድ አምላክ፤ በአካል፤ በስም፣ በግብር ሦስት፤ በመለኮት አንድ የሆነ አንድ እግዚአብሔር አብ ወልድ መንፈስ ቅዱስ መሆኑን አምና ታሳምናለች፤ ተምራ ታስተምራለች፡፡ ስለ እግዚአብሔር አንድነትና ሦስትነት፤ ፈጣሪነትና መጋቢነት... የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ባላት ኦርቶዶክሳዊ አስተምህሮ መሰረት ከአምስቱ አእማደ ምሥጢር አንደኛውን ክፍል ምሥጢረ ሥላሴን እንመለከታለን፡፡ ሥላሴ ማለት ሠለሰ ሦስት አደረገ ከሚለው የግዕዝ ግሥ የተወሰደ ሲሆን ትርጓሜውም ሦስት ሦስትነት ማለት ነው ተጨማሪ ያንብቡ፡፡

ምሥጢር ማለት ቃሉ የግሪክ ቋንቋ ሆኖ ቃሉ ከግዕዝና ከአማርኛ በቀጥታ የተወረሰ ሲሆን ትርጉሙም ድብቅ ፣ ስውር፣ ሽሽግ፣ ረቂቅ ፣ ለቅርብ ዘመድ ካልሆነ በቀር የማይገለጥ ማለት ነው፡፡ ለሁለት የሚከፈል ሲሆን ይኸውም የፍጡር ሚሥጢርና የፈጣሪ ሚስጥር በመባል ይታወቃል፡፡ የፍጡር ምስጢር ሁለት ይዘት አለው፡፡ የሰውና የመላዕክት ምስጢር ይባላል፡፡ በቤተክርስቲያን ውስጥ የሚገኘው የፈጣሪ የእግዚአብሔር ሚስጥር ይህ የከበረ የተወደደ የሚናፈቅ የበረከት ስጦታ ነው፡፡ ብርሃነ አለም ሀዋርያው ቅዱስ ጴጥሮስ እንዲህ ሲል በከበረ ቃሉ ገልፆታል፡፡ “እርሱንም ሳታዩት ትወዱታላችሁ አሁንም ምንም ባታዩት በእርሱ /በክርስቶስ/  አምናችሁ የእምነታችሁን ፍጻሜ እርሱን የነብሳችሁን መዳን እየተቀበላችሁ በማይናገርና ክብር በሞላበት ሀሴት ደስ ይበላችሁ”፡፡ በማለት ስውር ረቂቅ ከሆነው ጸጋ እግዚአብሔር የምንሰጠው ሀብት መሆኑን በማብራራት ገልፆታል፡፡ በዚህ መሰረት በቤተክርስቲያናችን ውስጥ ከሚፈጸሙት ሚስጥራት በቁጥር 7 ተወስነው ተቀምጠዋል፡፡ ውሳኔነታቸው ለሰባቱ ሰማያት ስብዐተ እግዚአብሔር ለማይከፈልባቸው ከተሞች ገላጭ ናቸው፡፡ እነዚህ ሰባት ሚስጥራት ቤተክርስቲያን የሚስጥርነታቸው ምክንያት በአይናችን ልናያቸው በእጃችን ልንዳስሳቸው የማንችል ልዩ ልዩ የመንፈስ ቅዱስ ስጦታዎች በእነዚህ ሚስጥራት አማካኝነት የሚሰጡን ስለሆነ ነው፡፡ አበው ሲናገሩ በንባብ የተሰወረ ብሂል ምስጢር ይባላል ብለው ስውርነቱን ረቂቅነቱን ይናገራሉ፡፡ ሰባቱ ሚስጥራተ ቤተክርስቲያን የሚባሉት እንደሚከተለው ይዘረዘራሉ። ተጨማሪ ያንብቡ፡፡

9999-1.png

መንፈሳዊ ህይወት

ትምህርተ ጦም በሊቃውንት

ምስል ወድምጽ

bottom of page